Weyera Primary and Middle School
Announcement GRADE 8 MINISTRY EXAM

GRADE 8 MINISTRY EXAM

19th June, 2026

ከተማ አቀፉ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ 22 የፈተና ጣቢያዎች በዛሬው እለት መሰጠት ጀምሯል ።


(ሰኔ 11/2018 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰኔ 11 እና ሰኔ 12/2018 ዓ.ም የሚሰጠው የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሚገኙ 22 የፈተና ጣቢያዎች ለ15,393 ተማሪዎች እየተሰጠ መሆኑን የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ ጽህፈት ቤቱ ፈተናው በሁሉም ጣቢያዎች ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀደም ብሎ የኮማንድ ፖስት ከማደራጀት ጀምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው ፈተናው በሚሰጥባቸው ጣቢያዎች የጸጥታ አካላትን ጨምሮ በቂ የፈተና አስፈጻሚዎች መመደባቸውን አመላክተዋል።

በክፍለ ከተማው ፈተናው እየተሰጠባቸው ከሚገኙ የፈተና ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነው መሰረተ እድገት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 648 ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር በመውሰድ ላይ መሆናቸውን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ተገኝ ታምሩ አስታውቀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with